ህትመቶች

ደንብ ቁጥር ፻፴፪/፪ሺ፲፬ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ

image description

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ ምክንያት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ድርጊቶችና ስጋቶች ላይ ተገቢ የሆኑ እርምጃዎችን በመውስድ አስቀድሞ መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ፤
የከተማውን ነዋሪ ህይወትና ንብረት እንዲሁም የልማት አውታሮች ደህንነት ከማንኛውም አደጋዎች እንዲጠበቅ ማድረግ እና ማናቸውም መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት ደህንነታቸው ተጠብቆ አስተማማኝ የሥራ አካባቢ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤
ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ህንጻ ተቀባይነት ባለው የአደጋ ደህንነት መከላከያ መስፈርት መሰረት አደጋን ሊቋቋም እና አደጋ ቢከሰት በተጠቃሚዎችና በአካባቢው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ሊቀንስ በሚችል መልክ ጥቅም ላይ ማዋል በማስፈለጉ፤
የአደጋ ስጋት ደህንነት መፈተሻ መሳሪያዎች አያያዝና የአደጋ ስጋት ደረጃ ማረጋጋጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፸፬/፪ሺ፲፬ አንቀጽ ፺፩ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡