ስለ እኛ

እንኳን ወደ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በደህና መጡ

Responsibility and Duties of the commission

1. By establishing an information and technology center, it will provide a centralized information exchange system before, during and after an accident, and serve as an information center for disaster risk management at the city level;
2. Collects information on the cause and level of vulnerability and analysis of natural and man-made disasters; Takes necessary early warning measures by conducting early risk indicator studies. He causes it to be taken. Follows up.

3. Works to prevent and reduce the damage caused by man-made or natural disasters; It makes other institutions work as well.
4. Makes institutions in the city include disaster risk reduction plans in their development plans; Monitors their implementation.
5. Organizes a training center where experts of the institution, various institutions and the public can receive training on disaster management.
6. Conducts sampling exercises on a regular or planned basis; It also facilitates the conditions for it to take place. Takes corrective action on the disaster response plan.

 

የቪዲዮ መግቢያ ስለ ድርጅቱ
image description

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራአመራር ኮሚሽን አጭር ታሪክ

  • image description

    አዲስ አበባ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራአመራር ኮሚሽን ምስረታ

    1926-1933 ዓ.ም

    የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተመሰረተው እንደ ኢትዮጲያ አቆጣጠር በ1926 ዓ.ም ሲሆን ስያሜውም እሳት አደጋ ማጥፊያ አገልግሎት ተብሎ ይጠራ ነበር፡፡ መስሪያ ቤቱም ይገኝ የነበረው አሁን ዋናው መስሪያ ቤት በሚገኝበት ቦታ ሆኖ የመጀመሪያው የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የነበረው ግለሰብም ስም ሚስተር ቱትር ቻኔኖቭ የሚባል ሩሲያዊ ዜግነት ያለው ነበር፡፡ በወቅቱም የነበሩት ሰራተኞች ብዛት 100ብቻ ነበሩ፡፡ በግዜው ያገለግሉ የነበሩ መሳሪያዎች ሁለት ላፊላ የውሃ በርሜል ተሸካሚ መኪኖች፣ አንድ በሰው ጉልበት የሚሰራ የውሀ መሳቢያና መርጫ ፓምፕ፣ ሁለት በማኔቤላ የሚዘጋና የሚታጠፍ ባለሁለት ጎማ በመኪና የሚጎተት መሰላል፣ አካፋ፣ ዶማ፣ መጥረቢያ የመሳሰሉት የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችና የአደጋ ጥሪ ይደረግ የነበረው በጩኸት በእግረኛ በእድር ጡሩንባ እንደነበረ ታሪክ ያስረዳል፡፡

  • image description

    የመስሪያ ቤቱ ስያሜው እና የሰው ሀይል በተመለከተ

    ከ1934 እስከ 1945 ዓ.ም

    ስያሜው የእሳት አደጋ ማጥፊያ አገልግሎት ተብሎ የቀጠለ ሲሆን የነበረው የሰራተኛ ወይም ሰው ሀይል 250 ሰራተኞች ነበሩ፡፡ የተቋሙ መሪ የነበሩትም ኃላፊዎች ማርሻል ሙሴ ስትዋርት እና ኢንጅነር ብራንካ የሚባሉ የውጭ ሀገር ዜጎች ነበሩ፡፡ ይገለገሉባቸው የነበሩትም ቁሳቁሶች ካላይ የተጠቀሱት እንዳሉ ሆነው በተጨማሪም ሶስት ፊያት የእሳት ማጠፊያ መኪኖች ነበሩት፡፡

  • image description

    ስሜያው የእሳት አደጋ ማጥፊያ ፖሊስ ብርጌድ ተብሎ ይጠራ የነበረ ሀላፊዎች ኢትዮጲያኖች የነበረበት ጊዜ

    ከ1946 እስከ 1973 ዓ.ም

    ስሜያው የእሳት አደጋ ማጥፊያ ፖሊስ ብርጌድ ተብሎ ይጠራ የነበረ ሲሆን ተቋሙ 250 ሰራተኞች ነበሩት፡፡ ኃላፊዎቼም ኢትዮጲያዊያን ሲሆኑ በዚህ ወቅት የነበረውን አደረጃጀት ስንመለከት አንድ ዋና መስሪያቤትና 6 ቅርንጫፍ ጣቢዎች የነበሩት ሲሆን፣ መገልገያ መሳሪያዎቹም 4 ፎምና ውሀ ተሸካሚ የእሳት ማትፊያ መኪናዎች፣ 2 ለፎቅ ቤት አደጋ ማጥፊያ የሚያገለግሉ መኪናዎች ነበሩ፡፡ በተጨማሪም ሶስት ፊያት የእሳት ማጠፊያ መኪኖችም ነበሩት፡፡

  • image description

    ስያሜው የእሳት አደጋ መከላከያና ማጥፊያ ፖሊስ ብርጌድ ተብሎ ይጠራ የነበረ ጊዜ

    ከ1974-1995 ዓ.ም

    ስያሜው የእሳት አደጋ መከላከያና ማጥፊያ ፖሊስ ብርጌድ ተብሎ ይጠራ የነበረ ሲሆን ተቋሙ 244 ሰራተኞች ነበሩት፡፡ ኃላፊዎቹም ኢትዮጲያዊያን ሲሆኑ በዚህ ወቅት የነበረውን አደረጃጀት ስንመለከት አንድ ዋና መስሪያቤትና 6 ቅርንጫፍ ጣቢዎች የነበሩት ሲሆን መገልገያ መሳሪያዎቹም 4 ፎምና ውሀ ተሸካሚ የእሳት ማጥፊያ መኪናዎች፣ 2 ለፎቅ ቤት አደጋ ማጥፊያ የሚያገለግሉ መኪናዎች ነበሩ፡፡

  • image description

    ስያሜው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች አገልግሎት የነበረ ጊዜ

    ከ1996 እስከ 2000 ዓ.ም

    ስያሜው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች አገልግሎት ሲሆን አደረጃጀቱም በአንድ ዋና መስሪያ ቤት እና በ 6 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ነበር፡፡ በወቅቱ የነበረውም የሰው ኃይል 280 ሰራተኞች፣ መገልገያዊቹም 1 ለፎቅ ቤት ቃጠሎ ማጥፊያ የሚያገለግል መኪና 8 የአደጋ መቆጣጠሪያ መኪናዎች እና 10 አቡላንሶች ነበሩ፡፡

  • image description

    ስያሜው እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል መቆጣጠር ኤጀንሲ ተብሎ ሲጠራ ነበር

    ከ2001 እስከ 2004 ዓ.ም

    ስያሜው እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል መቆጣተር ኤጀንሲ ተብሎ ሲጠራ የቆየ ሲሆን ተቋሙ የነበረውም የሰራተኞች ብዛት 554 ነበር፡፡ አደረጃጀቱም በ1 ዋና መስሪያ ቤትና በ7 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሆኖ መገልገያ መሳሪያዎቹም 8 ያደጋ መቆጣጠሪያ መኪኖች ፣15 አንቡላንሶች ፣3 ለፎቅ ቤት ቃጠሎ ማጥፊያ የሚያገለግሉ የአደጋ መቆጣጠሪያ ማሽኖች/ስካይ ሊፍት/1 የሪስኪው ቲምና

  • image description

    ስያሜው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ተብሎ ይጠራ የነበር

    2005 እስከ 2011 ዓ.ም

    ስያሜው የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ሲሆን የነበሩትም ሰራተኞች 1223 ሆኖ አደረጃጀቱም በ 1 ዋና መስሪያ ቤትና በ8 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ነበር፡፡ የመገልገያ ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎች 36 የእሳት አደጋ መቆጣተሪያ መኪኖች/ ፋየር ትራክ/ 3 ሃይድሮ ሊክ ሊፍትተሸካሚ ማሽነሪ፣ 1 ማስተር ሊፍት፣ 1 ክሬን 2 ሪስኪው ቡድንና 34 አንቡላንሶች እና ሌሎች 39 ተሸከርካሪዎች ነበሩት፡፡

  • image description

    ስያሜው የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው

    ከ2011 እስከ 2016 ዓ.ም

    ስያሜው የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሲሆን አጠቃለይ ያለው ሰራኞች 1558 ነው‹፡፡ አደረጃጀቱም በ1 ዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም በ10 ቅርንጫፍ ጽ/ቤትና 1 የእሳት አደጋ ሰራተኞች ማሰልጠኛ ማዕከል አለው፡፡ የመገልገያ መሳሪያዎችን ስንመለከት ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎች 64፣ 4 ክሬኖች፣ 2 ሪስኪው ቲም ፣ 34 አቡላንሶች፣ 6 ኮማንድ ካሮች፣10 ብረሽ የጎርፍ አደጋ መስሪያ መኪናዎች እና 48 የሚደርሱ ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ተስከርካሪዎች የከተማዋን ህብረተሰብ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

የጎብኚዎች አስተያየት

ምንም አልተገኘም.

የኮሚሽኑ መዋቅር

ተልዕኮ

Addis Ababa is to make disaster risk management a city where disaster safety is guaranteed by providing quality access to disaster risk management services.

ራዕይ

To see Africa's cities as the leading disaster management services provider by 2022.

እሴቶች

1. Respect and enforce professional ethics

2. Giving priority to safety and life

3. Risk-based development

4. Believe in teamwork

5. Doing bravery and adventure

6. Provide integrated and superior service

7. Fast and effective response

8. Community service