ህትመቶች

ይህ ደንብ “በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አደረጃጀት እና የፓራሚሊተሪ ሠራተኞች አስተዳደር ሥርዓት ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር146/2015’’ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

image description

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተፈጥሮ ወይም በሰው ሰራሽ ሊደርሱ የሚችሉ የድንገተኛ አደጋዎችን አስቀድሞ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ፤ አደጋ በሚከሰትበት ወቅት ውጤታማ የሆነ የአደጋ ምላሽ በመስጠት ህይወትና ንብረት ለማዳን እንዲሁም በአደጋ ምክንያት ለተጎዱ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለመስጠት እና በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢኖረውም የአደጋ ሠራተኛው በፓራ ሚሊታሪ ስርዓት ትዕዛዝ ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
በመሆኑም የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ተግባራትን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመምራት አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ የአደጋ ሠራተኞችን አስተዳደር መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀፅ 41 ንዑስ አንቀፅ 20 እና 91 መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡