የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የ IS...

image description
- ሁነቶች fire disaster    0

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የ ISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ስርአት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገኘ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የ ISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ስርአት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገኘ

 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 02/2018 ዓ/ም፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የ ISO 9001:2015 የጥራት መስፈርቶችን በማሟላት ዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ስርአት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገኘ፡፡ 

 

በመርሃ ግብሩ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ዲማ ነገዎ ባስተላለፉት መልዕክት ኢመደአ በዛሬው እለት ያገኘው የ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ስርአት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አስተዳደሩ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልእኮ በብቃት እንዲወጣ ትልቅ አቅም የሚፈጥርለት እንደሆነ ገልጸው፤ ለአስተዳደሩ አመራር እና አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የተቋም ዘላቂነትና ተሻጋሪነት የሚረጋገጠው በተሰማራበት መስክ የመወዳደሪያ አቅም ፈጥሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን ሲቻል ነው:: ይህንን ታሳቢ በማድረግ በተሰማራንበት የሳይበር ኢንዱስትሪ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች የጥራት ልህቀት ለማረጋገጥ የ ISO 9001፡2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓትን ተግባራዊ አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል:፡ ከዚህ አኳያ ይህንን የጥራት ስራ አመራር ስርዓት እውቅና ስንቀበል፣ ለጥራት የምንሰጠው ትኩረት መጨረሻ ደረጃ ደርሰናል ማለት ሳይሆን ወሳኝ የመታጠፊያ ነጥብ ላይ እንዳለን በመገንዘብ የተተገበረው ስርዓት ተቋማችን በተሰማራበት የሳይበር ምህዳር ተለዋዋጭነት እራሱን እያላመደ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለምናደርጋቸው ምርቶች እና አገልግሎቶች ሁሉንም የቁጥጥር፤ የህግ እና የደንበኞችን ፍላጎት መሻሻልን በቀጣይነት ታሳቢ በማድረግ ነው ሲሉ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገልጸዋል፡፡   

 

በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የ ISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ስርአት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለኢመደአ የሰጡት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መአዛ አበራ ባስተላለፉት መልዕክት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የ ISO 9001፡2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት አስፈላጊ መስፈርቶችን በአግባቡ በመተግበር የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘቱን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ አኳያ አስተዳደሩ የ ISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ስርአት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘቱ የአሰራር ሂደቶችን በቀጣይነት ለማሻሻል፣ ቅልጥፍናን ለማሳደግ፣ ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን የማረጋገጥ አቅሙን ለማሳደግ፣ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች የደንበኞችን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ለመስጠት በአጠቃላይ በተሰማራበት ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ተቋም እንዲሆን የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የ ISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ስርአትን ተግባራዊ በሚያደርግበት ሂደት በአማካሪነት ያገለገለው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ሲሆን፤ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት በቀለ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ISO 9001፡2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት እስካሁን ከሰላሳ አምስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሁለት በላይ (35,932) የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተቋማት ላይ የተተገበረና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው መስፈርት መሆኑን ገልጸዋል። ይህንን የምስክር ወረቀት ማሳካት ወጥነት ያለው፣ አስተማማኝ እና ደንበኛን ያማከለ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያግዛል። ከዚህ አኳያ ኢመደአ ይህንን የምስክር ወረቀት ማግኘቱ የክብር ባጅ ብቻ ሳይሆን የሀገራችንን የመረጃ ሀብት ለመጠበቅ ቀጣይነት ያለው መሻሻል እና የላቀ ብቃት ቁርጠኝነትን ማሳያ ነው ብለዋል።  

 

በሌላም በኩል በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊ ት ዳዊት፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የ ISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማግኘቱ ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ የሚሆን እንደሆነ ገልጸው፤ ለመላው የአስተዳደሩ አመራርና አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

 

በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ የ ISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ስርአት ትግበራ ሂደት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማት እና ግለሰቦች የምስጋናና የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷል፡፡

 

ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡- 

• ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et 

• ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA  

• ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@insa_et?_t=8qBKkyp092r&_r=1 

• ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@cyberigna1003/featured 

• ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet 

• ትዊተር (X) ፦ https://twitter.com/INSAEthio

• ሊንክድኢን:- https://www.linkedin.com/company/information-network-security-administration/ 

• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት፡- ነጻ የስልክ መስመር 933