በመዲናችን አዲስ አበባ በዲጂታል ቴክኖሎጅ እየተሰጠ ያለውን የነዋሪዎች የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ወደ ላቀና የተቀናጀ ዘመናዊ ስርአት ከፍ የሚያደርግ አዲስ ሲስተም ትግበራ በቅርቡ ይፋ ሊደረግ ነው።
በመዲናችን አዲስ አበባ በዲጂታል ቴክኖሎጅ እየተሰጠ ያለውን የነዋሪዎች የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ወደ ላቀና የተቀናጀ ዘመናዊ ስርአት ከፍ የሚያደርግ አዲስ ሲስተም ትግበራ በቅርቡ ይፋ ሊደረግ ነው።
በም/ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት በከተማችን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት ረገድ እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት በይበልጥ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልጽነት የተላበሰ እንዲሁም ተደራሽ የማድረግ አላማ ይዞ እየለማ ያለው አዲሱ ሲስተም የደረሰበትን ደረጃ ከጽ/ቤቱና ከኤጀንሲው አመራሮች ጋር በመሆን በዛሬው እለት ገምግመዋል።
በዚሁ መድረክ አዲሱን ሲስተም እያለማ ያለው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ቡድን ባቀረቡት ገለጻ አዲሱ ሲስተም ቀደም ሲል አልፎ አልፎ ያጋጥም የነበረውን የአገልግሎት መቆራረጥ ችግር የሚቀርፍ፣ በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶችን በሌሎች ተቋማት ከሚሰጡ ወሳኝ አገልግሎቶች ጋር አቀናጅቶ ለመጠቀም የሚያስችል፣ነዋሪዎችም አገልግሎቶችን ካሉበት ቦታ ሆነው እንዲያገኙ የሚያስችል፣ ዘመናዊና ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሆነ አብራርተዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት በከተማችን እየተሰጠ ያለው የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎቶች በሌሎች ተቋማት ዘንድ እንደ አብነት የሚጠቀስ እንደመሆኑ ይህንኑ አገልግሎት ከመዲናችን የስማርት ሲቲ ግንባታ ጋር የተዋኸደ፣ የተናበበና ዘመኑን በሚዋጅ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ መሠረተ ልማት ማሻሻያ ስራዎች የታገዘ፣ በየጊዜው እየላቀ እንዲሄድ እየተደረገ ባለው ጥረት የአዲሱ ሲስተም ትግበራ ከፍ ያለ ሚና እንዳለው አስምረውበታል።
አክለውም አዲሱ ሲስተም የከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጥ የመዲናዋን ሁለንተናዊ አድገትና ዘመናዊነት የደረሰበትን የእድገት ደረጃ የሚመጥን እንዲሆን ለማድረግ እየተካሄደ ባለው ጥረተ አብነታዊ ማሳያ በመሆኑ ሲስተሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተያዘው እቅድ ወደ ትግበራ ለማስገባት በሁለቱ ተቋማት ለተከናወኑ ስራዎች ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና ገልጸዋል። በቅርብ ቀናት ውስጥም የአዲሱን ሲስተም ትግበራ ይፋ ለማድረግ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንዲጠናቀቁም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager