አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ዙሪያ ከጸጥታ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ዙሪያ ከጸጥታ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለተወጣጡ አምስት
መቶ የፖሊስ አመራርና አባላት አደጋን አስቀድሞ በመከላከልና መቆጣጠር ዙርያ ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናውን የሰጡት በኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ጥናትና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ዴሲሳ ጦና እንደተናገሩት ኮሚሽኑ አደጋን አስቀድሞ በመከላከል እና አደጋ በአጋጠመ ጊዜ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በትብብር እየሠራ መሆኑን አስታውሰው በዛሬው ዕለት የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በተሻለ ትብብር ቅንጅት ለመስራት እንደሚያስችላቸው አብራርተዋል ።
የኮሚሽኑ አደጋ ቅነሳ ዘርፍ በከተማው ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት ፣ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የጸጥታ አካላት በአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ተከታታይ የሆነ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ለእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!