በአደጋ ስጋት ይህንነት ደንብና መመሪያ ላይ ለደ...

image description
- ሁነቶች training    0

በአደጋ ስጋት ይህንነት ደንብና መመሪያ ላይ ለደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በአደጋ ስጋት ይህንነት ደንብና መመሪያ ላይ ለደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከተማዋን ከአደጋ ስጋት የተጠበቀች ለማድረግ በሚያስችለው የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 ላይ እና ደንቡን ለማስፈጸም የወጣዉን መመሪያ ቁጥር 163/2017 አስመልክቶ ለአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ለማዕከል ከፍተኛ አመራሮችና ለአስራ አንዱም ክፍለ-ከተማ ስራ አስኪያጆች ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዉን ያስጀመሩት የኮምሽኑ ም/ ኮሚሽነርና የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ ደሳለኝ ፉፋ እንደተናገሩት ኮሚሽን መ/ቤቱ በከተማዉ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ማሟላት እንደሚጠበቅባቸዉ ጠቅሰዉ ይህን አደጋን ለመቀነስ የሚያስችለዉን ደንብ በማያከብሩ ተቋማት ላይ በደንቡ የተቀመጠዉን የማስተካከያ  እርምጃ ለማስፈጸም እንዲቻል  
የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ስልጠናዉ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

ም/ ኮሚሽነሩ አያይዘውም ማናቸውም ተቋማት አደጋን የመከላከልጉዳይን  የዕቅዶቻቸው አካል አድርገው መስራት እንደሚጠብቅባቸው  በማስታወስ ለአደጋ ቅነሳ ስራ 
እገዛ የሚያደርገውን ደንብ አለማክበር ለቅጣት የሚዳርግ በመሆኑ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳ ስበዋል። 

ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ያጸደቀውን ይህንን ደንብ ለማስፈጸም እንዲቻል ከአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በትብብር ለመስራትየሚያስችል  የጋራ መግባቢያ ሰነድ የተፈራረሙ ሲሆን ደንቡን አስመልክቶ በዛሬዉ እለት መሰጠት የተጀመረዉ ስልጠና ለሌሎች የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለምያዎች እንደሚሰጥም ተመላክቷል።

ኮሚሽኑ ደንቡ ተፈጻሚ እንዲሆን ከማድረጉ አስቀድሞ ለተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት በተለያዩ መድረኮችና የሚዲያ አግባቦች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ተመላክቷል ።

ለእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!