አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር ወሳኝ ቢሆንም ተቀናጅቶ ከመስራት አንጻር ውስንነቶች እንዳሉ ተገለጸ ።
አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራር ወሳኝ ቢሆንም ተቀናጅቶ ከመስራት አንጻር ውስንነቶች እንዳሉ ተገለጸ ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በከተማው ሊያጋጥሙ የሚችሉ እሳትና ሌሎች ደንገተኛ
አደጋዎችን አስቀድሞ በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የተከናወኑ ቅንጅታዊ አሰራሮችን አስመልክቶ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከባለድርሻ ተቋማት ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂዷል ።
ለውይይት መነሻ የ1ኛ ሩብ ዓመት ቅንጅታዊ አሠራር ሪፖርት
የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሰነድ መነሻነት የባለድርሻ ተቋማት ተወካዮች በሰጡት አስተያየት አደጋን ለመቀነስ በሚረደረገው ጥረት የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት ለመወጣት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልጸው በተለይም የተቋማቸውን የስራ ባህሪ መነሻ ያደረጉና ለአደጋ የሚያጋልጡ አሠራሮችን በመለየት ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር እየሠሩ መሆኑን አብራርተዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት ም/ ኮሚሽነርና የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ ደሳለኝ ፉፋ እንደተናገሩት አደጋን ለመቀነስ የሚከናወኑ ተግባራትን በጋራ ለመፈጸም ተቋማት የአደጋ ቅነሳ ስራን የእቅዶቻቸው አካል አድርገው መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ረገድ ኃላፊነታቸውን የሚወጡ ተቋማት ቢኖሩም አንዳንድ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተገቢው ካለመወጣቸውም በላይ የአደጋ ቅነሳ ስራውን ለመገምገምና ቅንጅታዊ አሠራሮችን ለማሻሻል በሚጠሩ መድረኮች የማይገኙ ተቋማት እንዳሉ ገልጸዋል።
አያይዘውም ከተማዋን ከአደጋ የመጠበቅ የጋራ ኃላፊነታችንን ለመወጣት በሚደረጉ ጥረቶች በአንዳንድ ተቋማት የሚታዩ የተሳትፎ ውስንነቶች መሻሻል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡
በውይይት መድረኩ አዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት፣ የስራው ክህሎት ቢሮ፣ ንግድ ቢሮ፣ ሀይማኖት ተቋማት ፣ደንብ ማስከበር፣ ህብረተሰብ ተሳትፎ፣ ጽዳት አስተዳደር ተሳትፈዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳወቁ!