የፈረንሳይ ሊዮን ከተማ የእሳት አደጋ መከላከል...

image description
- ሁነቶች fire disaster    0

የፈረንሳይ ሊዮን ከተማ የእሳት አደጋ መከላከል አገልግሎት ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተገኝተዉ ጉብኝት አካሄዱ።

የልዑካን ቡድኑ አባላት የኮሚሽኑን ዋና መ/ቤትና የአራዳን ቅርንጫፍ የጎበኙ

ሲሆን በጉብኝት መርሀ -ግብሩ ላይ በኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና በባለሞያዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

በዚሁ ጌዜም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ እንደተናገሩት ኮሚሽን መ/ቤቱ አዲስ አበባ ከተማ ከአደጋ የተጠበቀች ሰላማዊ ከተማ እንድትሆን በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዉ የሊዮን ከተማ የእሳት አደጋ መከላከል አገልግሎት ካለዉ ልምድና አቅም አንጻር በተለያዩ አግባቦች ኮሚሽን መ/ቤቱን እንዲደግፍ ጠይቀዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በጉብኝታቸዉ ሰፊ መረጃዎችን እንዳገኙ ጠቅሰዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ ያሉበትን ዉስንቶች ለመሙላት አስፈላጊዉን ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸዉ የገለጹ ሲህን በቀጣይ በሚኖሩ

ግንኙነቶች የድጋፎቹ አይነት እንደሚወሰኑ አብራርተዋል።