የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተልዕኳቸዉን ለመወጣት የሚያስችላቸዉ ምቹ የስራ ቦታ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎሮም ስራዎችን ዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጉብኝት አካሂደዋል።
በጉብኝት መርሀ ግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት በኮሚሽኑ የአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ፍቅሩ እንደተናገሩት በኮሚሽን መ/ቤት ደረጃ የተጀመሩና ወደተግባር የተገባባቸዉ የሪፎርም ስራዎች በአራዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ም እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰዉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከሚሸፍናቸዉ ወረዳዎች ጋር ካሉ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት ጋር በተለይም አደጋን አስቀድሞ መከላከል ረገድ ተከታታይ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
አቶ አለማየሁ አያይዘውም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እያከናወናቸዉ ለሚገኙ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ዎች የአራዳ ክፍለ-ከተማ አስተዳደር እያደረገላቸዉ ለሚገኘዉ ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
አቶ ጌታሁን አበራ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ከጉብኝቱ በኋላ እንደተናገሩት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በተለይም ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር አንጻር የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎች እጅግ አበረታች እንደሆነ ጠቅሰዉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ድጋፍ ሰጪ ባለሞያዎች ተልዕኮው ኳቸዉን ለመፈጸም ምቹ የስራ አካባቢ ወሳኝ በመሆኑ ክፍለ-ከተማዉ የተጓደሉ የስራ ክፍሎችን እንደሚያሟላ አረጋግጠዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!