ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ያልሆኑና ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮች እንዲታረሙ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች "የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጉላት አካታች እና ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ " በሚል መሪ ቃል ዓለም ዓቀፉን የአካል ጉዳተኞች ቀንን ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በልዩ ልዩ መርሀ-ግብሮች አከበሩ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳና በኮሚሽኑ የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሊቆዲሞስ ቡቼ እንደተናገሩት አካል ጉዳተኞች እንደማንኛዉም የህብረተሰብ ክፍል ለሀገሪቷ እድገትና ብልዕግና የራሳቸዉን አሻራ እያስቀመጡ ያሉ መሆኑን ጠቅሰዉ በተለያዩ አገልግሎት መስጫና የህዝብ መገልገያ ስፍራዎች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ያልሆኑና ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮች ላይ የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲወሰድ በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ለአቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች የገናን በዓል ምክንያት በማድግ የማዕድ ማጋራት ተካሂዷል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!