የአደጋ ጌዜ ልምምድ በእዉነተኛ አደጋ ጊዜ የተቀ...

image description
- ሁነቶች training    0

የአደጋ ጌዜ ልምምድ በእዉነተኛ አደጋ ጊዜ የተቀናጀና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችል ተገለጸ።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በመጪዉ ጥር ወር የሚካሄደዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ያለምንም አደጋ ክስተት እንዲጠናቀቅና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ሁለን አቀፍ አደጋ ጊዜ ልምምድ በህብረቱ ዋና መ/ቤት ዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም አካሄደ።

የኮሚሽኑ የአደጋ ምላሽ ዘርፍ ከአፍሪካ ሴፍቲና ሴኩሪት ሰርቪስ ጋር በመቀናጀት በእሳትና በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ላይ ያተኮረ ህይወትና ንብረት የማዳን የሚያስችል የተግባር ልምምድ ተካሂዷል።

በልምዱ ማጠቃለያ ላይ የአፍሪካ ህብረት ሴፍቲና ሴኩሪቲ ዲፓርትመንት ኃላፊ ኮሚሽነር አበራ ጸጋዬ እንደተናገሩት አደጋ ከማጋጠሙ በፊት መሰል ልምምዶችን ማካሄድ እዉነተኛ አደጋ በአጋጠመ ጊዜ የአደጋ ምላሽ አሰጣጡን ፈጣንና የተቀናጀ እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል።

በልምምዱ ላይ የእሳትና አደጋ ስጋት ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአምቡላንስ አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ቡድን እና አፍሪካ ህብረት የሴፍቲና የሴኩሪት ሰርቪስ ዲፓርትመን አባላት ተሳትፈዋል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!