ኮሚሽኑ በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ የጀመራቸዉ ስራዎች አ...

image description
- ሁነቶች training    0

ኮሚሽኑ በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ የጀመራቸዉ ስራዎች አበረታች ለዉጥ ማምጣታቸዉ ተገለጸ።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶችን ለማዘመን እንዲያስችለዉ የጀመራቸዉ የቴክኖሎጂ ትግበራ ስራዎች በኢትዮ ቴሌኮምና በኢንቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ እንዲሁም በአባያ ኩባንያ ከፍተኛ ኃላፊዎች ዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ተጎብኝቷል።

በጉብኝት መርሀ-ግብሩ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ቴክኖሎጂ ኦፊሰር አቶ ታሪኩ ደምሴ እና የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ እንዲሁም ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለሞያዎች ተገኝተዋል።

የስራ ኃላፊዎቹና ባለሞያዎች ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ኮሚሽን መ/ቤቱ አገልግሎቶቹን ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ የጀመራቸዉ ስራዎች አበረታች ለዉጦች ማምጣታቸዉን እንደተመለከቱ ገልጸዉ ቀሪና ያልተጠናቀቁትን የቀጣይ ምዕራፍ ስራዎችን ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ኮሚሽን መ/ቤቱ ከአዲስ አበባ ኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር አገልግሎቶቹን ለማዘመን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ዉል ገብቶ ወደስራ እንደገባም ተመላክቷል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!