"የሴት ጥቃት የኔም ነው፤ ዝም አልልም" በሚል...

image description
- ሁነቶች training    0

"የሴት ጥቃት የኔም ነው፤ ዝም አልልም" በሚል መሪ ቃል የነጭ ሪቫን ቀን ተከበረ።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር "የሴት ጥቃት የኔም ነው፤ ዝም አልልም " በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፉን የነጭ ሪቫን ቀን ዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በልዩ ልዩ መርሀ ግብሮች አከበረ ።

ዕለቱን በማስመልከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡት አዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህፃናት መብትና ደህንነት ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ራሄል መሉጌታ እንዳብራሩት የሴቷን ደህንነትና መብት እንዲሁም ተጠቃሚነቷን ማስጠበቅና መጠበቅ እንደሚገባ ጠቅሰዉ የሴትን ጥቃት መከላከል የሁሉም ኃላፊነት እንደሆነ ጠቁመዋል።

በመረሀ ግብሩ ላይ ዕለቱን አስመልክቶ ስነ-ግጥም የቀረበ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ለእሳትና ለሌሎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!