ህብረተሰቡ ጥንቃቄን ባህሉ እንዲያደርግ የበጎ ፈ...

image description
- ሁነቶች training    0

ህብረተሰቡ ጥንቃቄን ባህሉ እንዲያደርግ የበጎ ፈቃደኞች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለጸ።

በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከክፍለ-ከተማዉ አስተዳደር ጋር በመተባበር በአደጋ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ከክፍለ-ከተማዉ ለተዉጣጡ 650 ነባር በጎ ፈቃደኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል ።

በስልጠናዉ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጉለሌ ክፍለ-ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ አንደተናገሩት አዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ የልማት ስራዎች ላይ እንደምትገኝ አስታዉሰዉ እነዚህን የልማት ስራዎች ሊያጋጥሙ ከሚችሉ ድንገተኛ አደጋዎች ለመከላከል

በሚደረገዉ ጥረት ህብረተሰቡን በማስተማር ረገድ የበጎ ፈቃደኞች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አብራርተዋል።

በኮሚሽኑ የጉለሌ ክፍለ-ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሊቆዲሞስ ቡቼ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት

ህብረተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተረድቶ አደጋን አስቀድሞ እንዲከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን ጠቅሰዉ ይህንኑ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች በበጎ ፈቃደኞች እንዲታገዝ እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

አቶ ሊቆዲሞስ አያይዘዉ እንደተናገሩት ዛሬ የአቅም ግንባታ ስልጠና የተሰጣቸዉ ነባር በጎ ፈቃደኞች መሆናቸዉን በመጥቀስ በቀጣይ አዳዲስ በጎ ፈቃደኞች ተመልምለዉ ስልጠና እንደሚሰጣቸዉ ተናግረዋል።

በስልጠናዉ ማጠናቀቂያ ላይ በጎ ፈቃደኛ ሰልጣኞች በሰጡት አስተያየት በስልጠናዉ ያገኙትን ተጨማሪ እዉቀት ለህብረተረቡ በማድረስ አደጋን ለመከላከል እየተደረገ ያለዉን ጥረት በማገዝ ኃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!