ከአደጋ የተጠበቀ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር...

image description
- ሁነቶች fire disaster    0

ከአደጋ የተጠበቀ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማስቻል ተከታታይ የሆነ የግንዛቤ ማስጠበጫ ስልጠናዎች እንደሚያስፈልጉ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የቶዮታ ተሽከርካሪዎች አከፋፋይ የሆነው ሞኤንኮ ዘላቂ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስፋፋትና የደንበኞቹንና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለባለድርሻ አካላት ሰጥቷል።

የስልጠናዉ ዋና ዓለማም በነዳጅና እና በኤሌክትሪክ (ሀይብሪድ) እንዲሁም በኤሌክትሪክ ብቻ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች የአሰራርና ሂደታቸውን እንዲሁም በእነዚህ ሞዴሎች ላይ ሊከሰት የሚችሉ ማንኛቸውንም አደጋዎችን ለመቆጣጠር ስለሚሰጡ የአስቸኳይ ጊዜ የአደጋ ምላሾች የተሽከርካሪ አምራቹ የሚመራበትን የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ፕሮቶኮሎች ላይ ያተኮረ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ተሰጥቸቷል።

በዚህ ስልጠና ላይ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባለሞያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና የተሰጣቸዉ ሲሆን በቀጣይ መርሀ ግብር የባለድርሻ አካላት ለሆኑት ለድንገተኛ ህክምና ሰጪ ተቋማት፣ ለትራፊክ ፖሊስ ፣ ለኢንሹራንስና ለሌሎች ድርጅቶች ባለሞያዎችና ተመሳሳይ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የስልጠናዉ ተሳታፊዎች ከስልጠናዉ በኋላ በሰጡት አስተያየት በስልጠናዉ ሂደት ከዚህ ቀደም የማያዉቋቸዉን መረጃና ዕዉቀቶችን እንደጨበጡ ገልጸዉ እንዲህ ዓይነት ስልጠናዎች የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ አቅምን እንደሚያሳድግላቸዉ ተናግረዋል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!