መጪዉ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ያለአደጋ...

image description
- ሁነቶች fire disaster    0

መጪዉ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ያለአደጋ ክስተት በሰላም እንዲጠናቀቁ በሚያስችል ሰነድ ላይ ዉይይት ተካሄደ።

 

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች በመጪዉ ቀናት የሚከበሩት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ከማናቸዉም አደጋ ተጠብቀዉ እንዲከበሩ የሚያስችል ዉይይት ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም አካሂደዋል።

በዓላቱ የአደባባይ በዓላት በመሆናቸዉ በርካታ የሀገር ዉስጥ እና የዉጭ ሀገራት ዜጎች የሚታደሙበት በመሆኑ ከሚኖሩ ሰፊ መርሀ ግብሮችና እንቅስቃሴዎች አንጻር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ድንገተኛ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲያስችል በተዘጋጀዉ ሰነድ ላይ ሰፊ ዉይይት ተካሂዷል።

ኮሚሽን መ/ቤቱ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በሚከበሩበት ቦታ መርሀ-ግብሮቹ እስኪጠናቀቁ ድረስ አስፈላጊዉን ጥበቃ እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን በዓላቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ ከባለድርሻ የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ተመላክቷል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!