
ኮሚሽን መ/ቤቱ አዲስ አበባ ከተማ የደረሰችበትን ዕድገት የሚመጥን አገልግሎቶች እንዲሰጥ የተጀመሩ የሪፎሮም ስራዎች ዉጤት እያመጡ እንደሆነ ተገለጸ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የ2016 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸሙን የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አመራሮች እንዲሁም የኮሚሽን መ/ቤቱ አመራርና ሰራተኞች በተገኙቡት ዛሬ ነሀሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ተገምግሟል።
የግምገማ መድረኩ የመሩት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደተናገሩት ኮሚሽን መ/ቤቱ አዲስ አበባ ከተማ አሁን የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ የሚመጥን አገልግሎቶች ለመስጠት እንዲያስችለዉ ከመደበኛ ዕቅድ ተግባሮች ባሻገር የሪፎርም ስራዎች በመተግበራቸዉ በሁሉም ዘርፎች ዉጤት እንደተመዘገበ አብራርተዋል።
አቶ ተፈራ አያይዘዉም ኮሚሽን መ/ቤቱ በቀጣይ የከተማዋን ዕድገት ታሳቢ ያደረገ ዝግጁነት የሚያስፈገዉ በመሆኑ ለዚህም የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታዉቀዋል።
በግምገማ መድረኩ ሰራተኞች ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ከሰዉ ኃይል ከግብዓትና ጋር የተያያዙና ሌሎች አስተያየትና ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
ከሰራተኞቹ ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በየደረጃዉ ያሉ የኮሚሽኑ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በኮሚሽን መ/ቤቱ በርካታ አበረታች ተግባሮች ስለመከናወናቸዉ አንስተዉ በቀጣይ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የላቀ ዉጤት ለማስመዝገብ ሁሉም አመራርና ሰራተኞች እንዲተጋ አሳስበዋል።
በግምገማ መድረኩ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶበታል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!