በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት መልካም አስተዳደርን...

image description
- ሁነቶች fire disaster    0

በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ብልሹ አሰራሮችን ለመግታት በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ።

በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአስተዳደርና ፋይናንስ ስራ ክፍሎች በተጠናቀቀዉ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ረፖርት ቀርቦ በስራ ክፍሎቹ ያሉ አመራርና ባለሞያዎች በተገኙበት ዛሬ ሀምሌ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ተገምግሟል።

በሪፖርቱ ከቀረቡ ተግባራት መካከልም በበጀት ዓመቱ በተለይም ከግዢ ስርዓትና ከበጀት አጠቃቀም ጋር የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችና የታዩ ዉስንነቶች ቀርበዉ ሰፊ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።

በተያያዘም በቀጣይ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራት ዕቅድ ቀርቦ አስተያየቶች ከተሰጡ በኋለም ዕቅዶቹ የጋራ ተደርገዋል።

በዚህም መነሻም በቀጣይ 2017 ዓ.ም በጀት መልካም አስተዳደርን በማስፈንና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት በትኩረት እንደሚሰራም ተመላክቷል።

በመድረኩ በአስተዳደርና ፋይናንስ ስራ ክፍል ያሉ አመራርና ባለሞያዎች እንዲሁም የሁሉም ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ተሳትፈዋል።

ለእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳዉቁ::