በመንግስት ግዥ የህግ ማዕቀፍ ላይ ሲሰጥ የነበረ...

image description
- ሁነቶች training    0

በመንግስት ግዥ የህግ ማዕቀፍ ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በግዥና ከፋይናንስ አሰራር ስርዓት ጋር የሚታዩ የአቅም ዉስንነቶችን ለማሻሻል በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 17/2002 ፣ በመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 3/2002 እንዲሁም በመደበኛ የጨረታ ሰነድና በግዥ አፈጻጸም ማኑዋል ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ዛሬ ሀምሌ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል።

አቶ ዮሀንስ ዲሪባ የኮሚሽኑ የመንግስት ግዥ ዳይሬክተር የስልጠናዉን ዓላማ አስመልክቶ እንደተናገሩት ከግዢ ፣ከፋይናስና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የሚሰሩ አመራርና ባለሞያዎች የግዥና የክፍያ ስርዓቶች ለመፈጸም በህግ ማዕቀፉ የተመለከቱ ዝርዝር መመሪያዎች አዉቀዉና ተረድተዉ ስራቸዉን እንዲያከናዉኑ ለማስቻልና በዚህ ረገድ ቀደም ሲል ይታዩ የነበሩ የአሰራር ጉድለቶችን ለማረም እንደሆነ አስረድተዋል።

ስልጠናዉ የተሰጠዉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናስ ቢሮ በመጡ ባለሞያዎች ሲሆን የሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ፣ የማዕከል የግዥና ፋይናንስ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የጨረታ ኮሚቴ አባላት በስልጠናዉ ተሳትፈዋል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲ ሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!