በክረምት ጊዜ ሊያጋጥም ከሚችል የመብረቅ አደጋ እንዴት እራሳችንን መከላከል እንችላለን ❓
መብረቅ አደገኛ የተፈጥሮ ኃይል ሲሆን ፣ በደመና እና በመሬት መካከል በከባቢ አየር ውስጥ የሚፈጠር (የሚገኝ) ግዙፍ የኤሌክትሪክ ብልጭታ ነው።
መብረቅ በሚከሰትበት ወቅት በተለይም የስራ ባህሪያቸው ከቤት ውጭ የሆኑትን ሠራተኞች በእጅጉ ሊጎዳ ወይም ሊገድል ይችላል።
የመብረቅ አደጋ በአለም በየአመቱ ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ጊዜ ያጋጥማል፡፡
ባለፉት አምስት ዓመታት በአማካይ 850 የሚጠጉ ሰዎች በየዓመቱ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ለቋሚ የአካል ጉዳት ተዳርገዋል።
ከመብረቅ አደጋ እንዴት መከላከል ይቻላል?
ዝናብን ተከትሎ የሚከሰት ነጎድጓድ መብረቅን የሚያስከትል በመሆኑ የነጎድጓድ ድምጽ በሰማን ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ደህና መጠለያ ቦታ መግባት ያስፈልጋል፡፡
በረጃጅም ዛፎች ፣ በኮረብታዎች፣ በኤሌክትሪክ ምሶሶዎች፣ በስልክ ማማዎች፣ በአሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች አካባቢ መጠለል አደገኛ ነው፡
በሌላ በኩል ደግሞ በህንጻዎች ላይ የብረት ዘንግ መስቀል አደጋውን ለመከላከል የሚያስችል ሲሆን በር ዘግቶ በቤት ውስጥ መቆየት፣ ተሸከርካሪ ውስጥ ከሆኑ ደግሞ ከተሸከርካሪ አለመውረድ ይመከራል፡
ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ቀላል የጥንቃቄ እርምጃዎች በመተግበር እራስዎን ከመብረቅ አደጋ ይከላከሉ፡፡
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
All reactions:
77