ኮሚሽን መ/ቤቱ ለችግኝ መትከያ የሚዉል 11.8...

image description
- ሁነቶች fire disaster    0

ኮሚሽን መ/ቤቱ ለችግኝ መትከያ የሚዉል 11.8 ሄክታር ስፋት ያለዉ ቦታ ተረከበ

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር አካል የሆነዉን የችግኝ ተከላ ስራ ለማከናወን ከአዲስ አበባ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ተረክቧል።

ኮሚሽን መ/ቤቱ በየካ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 ፈረንሳይ አቦ ጸበል ጀርባ በሚገኘዉና 11.8 ሄክታር ስፋት የያዘዉን ቦታ ከተረከበ በኋላ ዛሬ ሀምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የቦታ ዝግጅትና የጉድጓድ ቁፋሮ ስራ አስጀምሯል።

በዚሁ መርሀ -ግብር ላይ የኮሚሽኑ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የችግኝ ተከላ ስራዉ በቀጣይ በሚኖረዉ መርሀ-ግብር ላይ መላዉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች የሚሳተፉበት እንደሆነም ተገልጿል።

የቦታ ርክክቡ የተካሄደዉ ከአዲስ አበባ ዉበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ጋር በተካሄደ ዉል ሲሆን በዉሉ መሰረትም ኮሚሽን መ/ቤቱ ከችግኝ ተከላ ጀምሮ ችግኞቹን እስከ መንከባከብ ድረስ ኃላፊነት የሚወስድ ይሆናል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ !