በክረምቱ የዕረፍት ጊዜ ወላጆች ለልጆቻቸዉ በቂ ጥበቃ ሊያደርጉ ይገባል።
በአዲስ አበባ ታዳጊዎችና ወጣቶች በቂ የዋና ችሎታ ሳይኖራቸዉ ዋና ለመዋኘት በሚል ወንዝ እየወረዱና ዉሀ በአቆሩ ጉድጓዶች ዉስጥ እየገቡ ህይወታቸዉን ያጣሉ።
በመሆኑም አሁን ላይ ትምህርት ቤቶች ዝግ በመሆናቸዉ በተለይም ታዳጊዎችና ወጣቶች ለጨዋታ በሚል ድርጊቱን የሚፈጽሙ በመሆኑ ወላጆች ለልጆቻቸዉ በቂ ጥበቃ ማድረግና ልጆቻቸዉን መምከር እንደሚገባቸዉ ተገልጿል።
በሌላ በኩልም የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አደጋዉን ለመከላከል ተከታታይ የሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶችን እያስተላለፈ በመሆኑ ህብረተሰቡ ፣ በተለይም ወላጆች እንዲሁም ታዳጊዎችና ወጣቶች ከኮሚሽን መ/ቤቱ እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እንዲተገብሩ ኮሚሽን መ/ቤቱ ያሳስባል።
በዛሬዉ ዕለት ሀምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ በቦሌ ክ/ከተማ
ወረዳ 12 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ዉሀ በአቆረ ጉድጓድ ዉስጥ ዋና ለመዋኘት የገባ የ13 ዓመት ታዳጊ ህይወቱ አልፏል።
የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች የታዳጊዉን አስከሬን አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ