በተጠናቀቀዉ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በአዲስ...

image description
- ሁነቶች training    0

በተጠናቀቀዉ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በአዲስ አበባና አካባቢዉ ከደረሱ አደጋዎች 37 ቢሊየን ብር ከዉድመት ማዳን መቻሉ ተገለጸ።

በተጠናቀቀዉ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት በአዲስ አበባና አካባቢዉ 523 አደጋዎች የአጋጠሙ ሲሆን ከደረሱት አደጋዎች መካከል 351 የእሳት አደጋ ሲሆኑ ቀሪ 172 አደጋዎች ደግሞ ከእሳት ዉጪ የአጋጠሙ ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ናቸዉ።በደረሱት አደጋዎች  የሁለት ሰዎች ህይወት በእሳት አደጋ ሲያልፍ የአደጋ ገዜ ሰራተኞችን ጨምሮ 90 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ደርሷል።በአጋጠሙት የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ ምክንያት ህይወታቸዉ አደጋ ዉስጥ የነበሩ 156 ሰዎችን ህይወት መታደግ የተቻለ ሲሆን  በሌላ በኩል ከ 37 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከዉድመት ማትረፍ ተችሏል።ከደረሱት 523 አደጋዎች ዉስጥ 465 በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ቀሪ 58 አደጋዎች በተለያዩ የሸገር ከተሞች የአጋጠሙ ናቸዉ።ከአምና ተመሳሳይ ጊዜ ከደረሱ አደጋዎች ጋር ሲነጻጸር በተለይም በሰዉ ሞትና ከአካል ጉዳት ጋር ሲነጻጸር ሞት በሰባት ሲቀንስ ጉዳት በሀያሶስት የቀነሰ ሲሆን ኮሚሽን መ/ቤቱ አደጋዎች ከደረሱ በኋላ በአደጋ ስፍራ ፈጥኖ በመድረስ የሰዉ ህይወትና ንብረት የማዳን አቅሙ እያደገ መምጣቱ ተገልጿል።